አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስቴር ለትግራይ ክልል መንግስት ጊዜያዊ አስተዳደር 10 ሚሊዮን ብርና የተለያየ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ለትግራይ ክልል መንግስት ጊዜያዊ አስተዳደር ኮንስትራክሽን፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ወደ መደበኛው እንቅስቃሴ ለመመለስ እንዲያስችለው የ10 ሚሊዮን ብር የገንዘብ የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ።
በትግራይ ክልል የተካሄደውን ህግ የማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በትራንስፖርት ዘርፍ ከፌዴራል ለክልል በዉክልና የተሰጡ ተግባራትን ጨምሮ በትራንስፖርት ዘርፍ መደበኛ መንግስታዊ ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ ወደ ስራ ለማስገባት እንዲቻል የ10 ሚሊዮን ብር እና የተለያዩ የስራ መገልገያ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታውቃል።
ድጋፉ የመንገድና ትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፉ ወደ ተጠናከረ ስራ እንዲገባ ከሀገራዊ የትራንስፖርት ዘርፍ መሪ ልማት ዕቅድ አንጻር ቢሮዉ ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ እንደሚያግዝ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ገልጸዋል።
የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽን፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አሉላ ሀብተአብ በድጋፉ ርክክብ ወቅት እንዳሉት የትራንስፖርት ሚኒስቴር የዘርፉን ችግር ለመቅረፍ በፍጥነትና በትክክለኛ ወቅት ድጋፍ አድርጓል።
በዚህም ችግራችንን በመገንዘብ ስራዉን ለመጀመር አስፈላጊ የሆኑ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በአጭር ጊዜ ዉስጥ በማድረጋቸዉ ምስጋና ማቅረባቸውን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

