Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ፣ ባለቤት አልባ ህንፃዎች፣ የኮንደሚኒየም ቤቶች፣ የቀበሌ መኖሪያና ንግድ ቤቶችን አስመልክቶ ውሳኔ አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ፤ ባለቤት አልባ ህንፃዎች፤ የኮንደሚኒየም ቤቶች፤ የቀበሌ መኖርያና ንግድ ቤቶችን አስመልክቶ በጥናት የተገኘው ግኝትቶች ላይ የውሳኔ አስተላለፈ፡፡

የከተማው ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የለውጥ አመራሩ ዘረፋና ሌብነትን ለመታገል በገባው ቃል  መሰረት ምንም እንኳ ቢዘገይም የነዋሪውን ቅሬታ መነሻ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት: በገለልተኛ አካል እና በተጨባጭ ጥናት ላይ በመመርኮዝ ማጣራቱ ይታወቃል፡፡

የተደረገውን ጥናት ግኝት መነሻ በማድረግ መወሰድ አለበት ባሉት እርምጃ ላይ አፅንኦት ሰጥቶ ተወያይተዋል፡፡

  1. በጥናቱ የተገኙ 322 ባለቤት አልባ ህንጻዎች የከተማ አስተዳደሩ እንዲወርስ እና በግልፅ ጨረታ ተሸጠው ገቢው ለህዝብ ልማት እንዲውል፤
  2. በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ : ባዶና ዝግ ሆነው የተቀመጡ 21,695 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን  ለ1997 ተመዝጋቢ የሆኑና በቋሚነት እየቆጠቡ ላሉ ነዋሪዎች በእጣ እንዲተላለፍ፤
  3. የቀበሌ መኖርያ ቤቶችን አስመልክቶ በህገ-ወጦች የተያዙ የመኖርያ ቤቶች ግልፅ የሆነ መስፈርት ወቶላቸው ለደሆች፤ ለአቅመ ደካሞችና ለተለያየ ችግር ለተጋለጡ የከተማው ነዋሪዎች እንዲሰጥ፤
  4. የቀበሌ የንግድ ቤቶች በህገ-ወጥነት ከያዙት ቤቶች አስለቅቆ ለስራ አጥ ወጣቶች በእጣ እንዲሰጥ ተወስኖአል፡፡
  5. ይህ እስኪከናወን ታግደው ባሉበት እንዲቆዩ ለፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ ውሳኔውን ማሳወቅ እንዳለባቸው፤

ካቢኔው በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ በሰፊው የተወያየ ሲሆን ይህ ችግር እና ስርዓት አልበኝነት  ከለውጡ በፊት  ከ1997 ጀምሮ የተፈፀመ በመሆኑ ወደፊት እንዳይደገም በፅናት እንደሚሰራ እና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ የተላለፈውን ውሳኔ የከተማው አቃቢ ህግ እየተከታተለ ሪፖርት እንዲያደርግ መወሰኑን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version