አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአል-ሸባብ ታጣቂዎች በሞቃዲሾ በሚገኝ ሆቴል ላይ በፈጸሙት ጥቃት የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
አፍሪክ በተባለውና በመዲናዋ በሚገኝ ሆቴል ላይ የተፈጸመው ጥቃት በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ ቦምብ የተጀመረ ሲሆን፥ ዘግየት ብሎም ታጣቂዎቹ ከፀጥታ አካላት ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገዋል፡፡
በጥቃቱም አራት ታጣቂዎችን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ 10 በላይ ሰላማዊ ሰዎች መቁሰላቸው ነው የተነገረው፡፡
ለህልፈት ከተዳረጉት መካከልም የቀድሞው የጦር ጄኔራል ሞሃመድ ኑር ጋላል ይገኙበታል ነው የተባለው፡፡
ሆቴሉ የሶማሊያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት መሰብሰቢያ መሆኑም ተነግሯል ፡፡
ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅትም በስፍራው በርካታ የመንግስት አካላት እና ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት እንደነበሩ ተገልጿል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

