Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ከአቡ ዳቢ ልማት ፈንድ መንግስታዊ ተቋም ዳይሬክተር ጄኔራል ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የኢፌዴሪ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ከአቡ-ዳቢ ልማት ፈንድ መንግስታዊ ተቋም ዳይሬክተር ጄኔራል መሐመድ ሰይፍ አል ሱዋዲ እና የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ።
በውይይቱ ወቅት ተቋሙ በኢትዮጵያ ለልማት ፕሮጀክቶች ድጋፍ ማድረግ በሚችልባቸው አሰራሮች ዙሪያ ምክክር ያደረጉ ሲሆን፥ የሃገራቱን የኢኮኖሚ ትብበር ለማጠናከር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያም ተወያይተዋል።
በተጨማሪም የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ተቋማት እና የግሉ ዘርፍ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ በሚችሉባቸው ዘርፎች ላይ መክረዋል፡፡
እንዲሁም በቀጣይ በኤምባሲው አስተባባሪነት ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፣ ከአቡ-ዳቢ ልማት ፈንድ፣ ከሃገሪቱ የግሉ ዘርፍ እና ከኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍና የመንግስት ተቋማት ጋር በመቀናጀት በቪዲዮ ኮንፈረንስ የታገዘ የኢንቨስትመንት እና የንግድ ፎረም ለማካሄድ በሚቻልበት መንገዶች ላይ ምክክር ማድረጋቸውን በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version