አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲከናወን ለጸጥታ ሁኔታዎች ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች አስታወቁ ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳውና የሀረሪ ክልል ርእስ መስተዳደር አቶ ኦድሪን በድሪ እንዳሉት ÷በምርጫው የሚሳተፉ የተፎካካሪ ፓርቲዎች በሰላማዊና በነጻነት በክልሎቹ የሚንቀሳቀሱበትና ዲሞክራሲያዊ ምህዳርን የመፍጠር ስራ እየተከናወነ ይገኛል ።
የደቡብ ክልል የምርጫ እቅድ ከወዲሁ በማውጣት ስራዎቸን የጀመረ ሲሆን ÷የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው እንደሚሉት በቅድመ ምርጫው ሆነ በምርጫው ወቅት ሊፈጠር የሚችል የጸጥታ ስጋትን አስቀድሞ የመቆጣጠር ዝግጀት እየተከናወነ ይገኛል ።
በክልሉ የጸጥታ መዋቀርም ከምርጫው አንጻር በማደራጀት ግጭት ያሉባቸውን ቦታዎች የመለየት ፣ከቀያቸው የተፈናቀሉትን መልሶ በማቋቋም በምርጫው የሚሳተፉበትን ሁኔታን የማመቻቸቱ ስራም ትኩረት ተሰጥቶታል ነው ያሉት።
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በማቋቋም የስነ ምግባር መርሆችን በማክበር እንዲሰሩ ጥረቶች መደረጋቸውንም ጠቅሰዋል ።
እንዲሁም የምርጫ ጣቢያዎች ዝግጅት ሂደት ላይ ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ክልሎች በቅንጀት እንደመስራታቸው የደቡብ ክልል ተገቢውን ቅድመ ሁኔታዎች እያመቻቸ ይገኛል ብለዋል።
የሃረሪ ክልል የክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ኦድሪን በድሪ በበኩላቸው በ6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ አካላት ሁሉ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱበትን ሁኔታ ለመፍጠር የክልሉ መንግስት በገለልተኝነት መረህ የጸጥታ ሀይሉን እያነጸ ይገኛል ብለዋል ።
ይህ መርህ ደግሞ ካለፉት ምርጫዎች አንጻር የተሻለ የዲሞክራሲያዊነት የተጎናጸፈ ሂደት ለማስፈጸም ያለን ቁርጠኝነት ያሳያል ነው ያሉት።
ከዚህ ቀደም በሀገሪቱ የምርጫ ክፉ ልማዶች የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትን የማሳደድ አለፍ ሲልም ያለ ጠያቂና ከልካይ አስሮ ማሰቃየት አይነት ኢ – ዲሞክራሲያዊ ተግባራት በቀጣዩ ምርጫ የማይታሰብ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ርእሳነ መስተዳደሮችም በ6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ጸጥታን ለማስፈን ህብረተሰቡም ተለምዷዊ ትብብሩን እንዲያደርግ ጠይቀዋል ።
በሀይለየሱስ መኮንን
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

