Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአማራ ክልል ለከፍተኛ ግብር ከፋዮችና ሠራተኞች የዕውቅና አሠጣጥ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል ሲካሄድ የነበረው ልዩ የግብር ንቅናቄ መድረክ የመዝጊያ መርሐግብር በባሕር ዳር ከተማ ክልል ምክር ቤት አዳራሽ ተካሄደ።
“ግልጽ አሠራርን እዘረጋለሁ፤ ተጠያቂነትን አሰፍናለሁ” በሚል መርህ ሲካሄድ የነበረው ልዩ የግብር ንቅናቄ መድረኩ ከጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ሲካሄድ ቆይቷል።
ከሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች የተውጣጡ የገቢ መሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፤ የግብር አከፋፈል አምባሳደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የልዩ ንቅናቄው ተሳታፊዎች ናቸው።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር÷ በከፍተኛ ግብር ከፋዮችና ሠራተኞች የዕውቅና አሠጣጥ መርሐ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
ሌሎች የቢሮ ኃላፊዎች፣ የግብር አምባሳደሮችና አዲስ የግብር አምባሳደር ተሿሚዎች በመድረኩ መታደማቸውን አብመድ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version