አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ በዲቦራ ፋዉንዴሽን ማእከል የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቤት ግንባታ አስጀመሩ።
የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በትኩረት ሊሰራበት ካስቀመጣቸዉ አቅጣጫዎች አንዱ የአይምሮ ጤና እንክብካቤ እና ደህንነት ነዉ፡፡
በመሆኑም በዲቦራ ፋዉንዴሽን ማእከል የአእምሮ ዉስንነት ላለባቸዉ ህጻናት እና ወጣቶች አገልግሎት የሚዉል ትምህርት ቤት ለመገንባት ዛሬ የመሰረት ድንጋይ እና ግንባታ የማስጀመር ስነስርአት አካሂዷል፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በዲቦራ ፋዉንዴሽን ለሚገነባዉ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቤት ፕሮጀክት 19 ሚሊየን ብር የመደበ ሲሆን÷ የፕሮጀክቱ የገንዘብ ምንጭ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለትምህርት ቤቶች ግንባታ ከሰጡት የመደመር መጽሀፍ ሽያጭ ነዉ ተብሏል፡፡
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው የመሰረት ድንጋይ ካስቀመጡና የግንባታ ማስጀመር ስነስርዓት ካካሄዱ በኋላ በማእከሉ ችግኝ መትከላቸውን ከቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

