አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዳይቋረጥ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዬን እጠቀማለሁ” በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የ“እንድናገለግልዎ ማስክ ያድርጉ” ንቅናቄ በትምህርት ቤቶች በይፋ ተጀምሯል።
ንቅናቄውን የትምህርት ሚኒስቴር ከጤና ሚኒስቴር፣ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል።
የትምህርት ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት እንዲሁም የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች በዳግማዊ ሚኒሊክ መሰናዶ ትምህርት ቤት በመገኘት ንቅናቄውን በይፋ አስጀምረዋል።
ንቅናቄው ከዛሬ ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኛው ገብሩ የመማር ማስተማሩ ሂደት እንዳይቋረጥ እና ትምህርት ቤቶች እንዳይዘጉ በትምህርት ቤት ውስጥ እና ከትምህርት ቤት ውጪ ተማሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን በአግባቡ ሊጠቀሙ ይገባል ብለዋል።
ከዛሬ ጀምሮም በትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን ማድረግ ልምድ ሊሆን እንደሚገባው በፕሮግሩሙ ላይ ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ ወይዘሮ ሐረጓ ማሞ በበኩላቸው በህብረተሰቡ ውስጥ መዘናጋት እየተስተዋለ እና የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየተስፋፋ በመሆኑ ሁሉም አካል የኮቪድ መከላከያዎችን በአግባቡ ሊጠቀም እንደሚገባ አውስተዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

