አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ታቦር ከተማ አጅባር ሜዳ ዓመታዊው የፈረስ ጉግስ እና ግልቢያ ጨዋታ ተካሄደ።
የፈረስ ጉግስ እና ግልቢያ ጨዋታው የመርቆሪዎስ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚደረግ ነው።
በዚህ ስነ ስርዓት ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የአማራ ክልልና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶችና የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።
የፈረስ ጉግስ ከጥንት አባቶች ከጠላት ጋር ተጋድሎ ያደረጉበት ታሪካዊ ሂደት ያለው በመሆኑ የሚከበር ነው ተብሏል።
ይህን የበዓል አከባበር ለሀገር የቱሪዝም መስህብ መጠቀም እንዲቻል አካባቢያውን ለማስተዋወቅ ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው አካላት ሊሰሩ እንደሚገባ መገለፁን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ፎቶ ፤ ከማህበራዊ ሚዲያ
የተባለው፡፡ ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

