አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ አርሲ ዞን ነንሰቦ ወረዳ ባጋጠመ የትራፊክ አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ሳጅን አህመድ ጠቀሳ እንዳታወቁት አደጋው የተፈጠረው ጠጠር የጫነ ሲኖትራክ በላዩ ላይ ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ በመገልበጡ ነው፡፡
የጭነት ተሽከርካሪው ከገደብ አሳሳ ወደ ነንሰቦ ወረዳ ሲጓዝ ከዶዶላ ወረዳ ሶሮታ ከተማ 21 ሰዎችን ጮኖ በፍጥነት ላይ እያለ በሁሩ ቀበሌ አሸዋ ወንዝ ወይም በለጩ ሲደርስ ተገልብጦ አደጋው ደርሷል፡፡
አደጋውም ትናንት ምሽት 4፡00 ሰዓት አካባቢ ያጋጠመ ሲሆን 16 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
ህይወታቸውን ካጡት መካከል ሰባቱ ህፃናት መሆናቸውን ሳጅን አህመድ ጠቀሳ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም 5 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል ብለዋል ኃላፊው፡፡
ከአደጋው ለተረፉ ሰዎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑንም ገልፀዋል::
የአደጋው መንስዔም ያለአግባብ በጭነት መኪና ህዝብን መጫንና ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በቢቂላ ቱፋ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

