አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕንድ የኢፈዴሪ ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ዶክተር ትዝታ ሙሉጌታ ከሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የልማት ትብብር አስተዳደር ቋሚ ተጠሪ አክሂሌሽ ሚሽራ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱ በዋናነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው ግንኙነት፣ ሕንድ በአቅም ግንባታና በልማት ፋይናንስ እያደረገች ባለው ድጋፍ እንዲሁም በኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር ፡፡
አምባሳደር ዶክተር ትዝታ ሙሉጌታሕንድ በአቅም ግንባታና በልማት ፋይናንስ እየሰጠች ላለው ድጋፍ አመስግነው በያዝነው የፈረንጆቹ አመትም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመጠየቅ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለትብብሩ ስኬት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
አምባሳደሯ ኢትዮጵያ በአይቴክ የሚሰጠውን የአቅም ግንባታ ድጋፍ ሙሉ ለሙሉ ለመጠቀም የላቀ ዝግጁነት እንዳላትም መናገራቸውን በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለጣቢያችን የላከው መግለጫ ያመላክታል።
ወቅታዊ የሃገሪቱን ሁኔታ በሚመለከትም በትግራይ ክልል የተካሄደው የህግ የበላይነትን የማስከበር ዘመቻ በተሳካ ሁኔታ ተካሂዶ መጠናቀቁን ገልፀውላቸዋል።
በህግ የሚፈለጉ የህወሓት ጁንታ ቡድን አባላትን በህግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን ማዳረስ፣ ጁንታው ያፈረሰውን መሰረተ ልማት መልሶ ግንባታ እና ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደርም በየደረጃው ያሉትን መዋቅሮች መልሶ በማደራጀት፣ ከህዝብ ጋር ውይይቶችን በማድረግ መረጋጋት ለማስፈን እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ከሱዳን ጋር የተፈጠረው የድንበር ውዝግብ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፍትሄ እንዲያገኝ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የልማት ትብብር አስተዳደር ቋሚ ተጠሪ አክሂሌሽ ሚሽራ በበኩላቸው÷ ሕንድ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
ለአቅም ግንባታና በአጭር ጊዜ ሁነኛ ለውጥ ለማምጣት በሚያስችሉ በተለይም ደግሞ ስራ አጥነትንና ድህነትን በመቅረፍ እንዲሁም የዕውቀት ሽግግርን በሚያሳልጡ ፕሮጀክቶች ላይ ማተኮር እንደሚገባም ነው የገለጹት፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

