አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ትምህርት የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ማድረጉን የቢሮ ኃላፊ አቶ ማሄ ቦዳ አስታወቁ።
በዚህም በሲዳማና በደቡብ ክልል ለፈታና ከተቀመጡ 352 ሺህ 806 ተማሪዎች ውስጥ ወደ 322 ሺህ 136 የሚሆኑት ወደ 9ኛ ክፍል መዛወራቸውን ተናግረዋል።
ይህም ማለፋቸውንና ይህም 91 ነጥብ 3 በመቶ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በማረም ወቅት መልስ መስጫ ወረቀት በትክክል ያለማጥቆር፣ የስም ስህተትና የመለያ ኮድ ስህትት የታዩ ችግሮች መሆናቸውንም አንስተዋል፡፡
ይህን ችግር እንግሊዝ ሀገር ካለው DRS ከሚባል ሶፍት ዌር ኩባንያ ጋር በመነጋገር መፈታቱንና በቀጣይ ይህ ችግር እንዳይገጥም ተማሪዎች መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ትኩረት ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቅሰዋል፡፡
በአጠቃለይ የማለፊያ ነጥቡ ኮቪድን ታሳቢ በማድረግ ለወንድ 41፣ ለሴት 40 እና ማየት ለተሳናቸው 39 ሆኑ ተወስኗል ማለታቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በተያያዘም የ9ኛ ክፍል ቅበላ በሁሉም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የካቲት 1 እና 2 ቀን ሲሆን ትምህርት የካቲት 3 ቀ 2013 ዓ.ም መሆኑንና ተማሪዎችም በተገለጸው ጊዜ አስፈላጊ ቁሳቁስ በማዘጋጀት ትምህርት ቤት እንዲገኙም ጥሪ አቅርበዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

