አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ለማሻሻል ወደ ተግባር የገባው የሊዝ ፋይናንስ ስርዓት የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ ሊሆን እንደሚገባው የግብርና ሚኒስቴር ጠየቀ።
የግብርና ሚኒስቴር ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በሊዝ ፋይናንስ ዙሪያ ተወያይቷል።
በውይይቱ በብሄራዊ ባንክ የተደረጉ የህግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎች ለዘርፉ ማደግ አስተዋጽኦ ቢያደርጉም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀራርቦ መስራት ወሳኝ ነው ተብሏል።
ባንኮች ከአጠቃላይ ብድራቸው 5 በመቶውን ለግብርና ሊዝ ፋይናንስ ማዋል ይገባቸዋል ቢባልም በዚህ ረገድ ግን ቁጥጥር ማድረግ ላይ ሊተኮር ይገባልም ተብሏል።
በምስክር ስናፍቅ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

