Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ከዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባዳር ሬድዋን ሁሴን ከዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ ልዑክ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ምክትል ሀላፊ አንድሬ ክሊሞቭ የተመራው ልዑክ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት አድርጓል፡፡

በዚህ ወቅት ልዑኩ የሁለቱን ሃገራት ፖለቲካዊ ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልበት አግባብ ላይ ምክክር አድርጓል፡፡

ከዚህ ባለፈም በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ዋና ሀላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያም ተወያይቷል፡፡

በዚህ ወቅትም ብልፅግና ፓርቲ ከሩሲያው ዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ አብሮ መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

የዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ምክትል ሀላፊ አንድሬ ክሊሞቭ ለሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባታቸውን የሩሲያ ኤምባሲ አስታውሷል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version