አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ከሩሲያ የቢዝነስ ልዑካን ጋር ተወያዩ።
የልዑካን ቡድኑ በግንባታ፣ በኢንዱስትሪ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና በሌሎችም ዘርፎች የተሰማሩ ኩባንያዎችን ያቀፈ የኢንቨስትመንት ቡድን ሲሆን በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፎች ለመሰማራት በሚችልባቸው እድሎች ዙሪያ ሰፊ ገለፃ ተደርጎለታል።
በተለይም በቤቶች ልማት ዘርፍ ያለውን ፍላጎትና የኢንቨስትመንት አቅም በተመለከተ ገለፃ የተደረገ ሲሆን መንግስት የዜጎችን የቤት ፍላጎት ለማሟላት ብዙ ርቀት ቢሄድም ክፍተቱን ለመሙላት የግልና የውጭ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለመጠቀም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ተመልክቷል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት በተደረገላቸው ገለፃ መደሰታቸውን በመግለፅ በኢትዮጵያ ከትርፍ ባሻገር እንደ ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች ባሉ ማህበራዊ መሰረተ ልማቶችን ባካተተ መልኩ መሰማራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ያላት የኢንቨስትመንት አቅም ሰፊ መሆኑን መረዳታቸውን በመጥቀስም በቅርቡ ወደተግባር ለመግባት የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል።
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ በበኩላቸው ከተሞች ከፍተኛ የልማት አንቀሳቃሽ ማዕከል መሆናቸውንና በከተሞች የቤቶች ልማት ዘርፍ ባለው የኢንቨስትመንት ዕድል እንዲጠቀሙ ጠይቀዋል።
የግንባታው ዘርፍ የኢንቨስትመንቶች ዋነኛ ምንጭ እንደመሆኑ በዘርፉ በኢትዮጵያ ቢሰማሩ እንደሚጠቀሙ ገልፀውላቸዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

