አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2013 (ኤፍቢሲ) 9ነኛው የበጎ ሰው ሽልማት የእጩዎች ጥቆማ ከየካቲት 1 ቀን ጀምሮ ከህዝብ መቀበል እንደሚጀመር ኮሚቴው ገለጸ፡፡
ለሃገርና ለህዝብ ዓርአያነት ያለው ታላቅ ተግባር ያከናወኑ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን በየዓመቱ ዕውቅና የሚሰጠው የበጎ ሰው ሽልማት በ2013 ለሚያካሂደው ዘጠነኛው መርሃ ግብሩ ነው የእጩዎች ጥቆማ የሚቀበለው፡፡
በስምንተኛው የበጎ ሰው ሽልማት አቶ ካሊድ ናስር፣ አቶ ኪሮስ አስፋው፣ ቢኒያም ከበደ፣ መሀመድ አልአሩሲ፣ ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ፣የሕክምና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች፣ ኢትዮ ቴሌኮም ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ በሰራቸው የበጎ አድራጎት ሥራዎቹ፣ በጉባ በሥራ ላይ የሚገኙ የህዳሴው ግድብ ሰራተኞች መሸለማቸው ይታወሳል፡፡
በ9ነኛው ሽልማት መርሃግብር በአስር ዘርፎች ከየካቲት 1 እስከ 30 ድረስ ጥቆማ እንደሚቀበሉ ነው የተገለጸው፡፡
- በመምህርነት
- ሳይንስ (ህክምና፣ ቴክኖሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ምህንድስና ኬሚስትሪ አርክቴክት እና ወዘተ
- ኪነጥበብ
- በጎአድራጎት
- ቢዝነስና ስራ ፈጠራ
- መንግስታዊ ተቊማት ኃላፊነት የሰራ
- ቅርስና ባህለ፤
- ማህበራዊ ጥናት
- ሚዲየቃና ጋዜጠኝነት
- ለኢትዮጵያ ዕድገት አስተዋፅዖ ያበረቱ ዳያስፖራዎች
ለጥቆማ የቀረበው ስልክ ቁጥር፡- +251977232323 (ቫይበር፣ ቴሌግራምና ኋትስአፕን ጨምሮ)፤
ኢሜይል፡- begosewprize@gmail.com
ፖስታ፡- 150035
የውብዳር ጌትዬ

