Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ ከጣልያን የቱሪዝም ዳይሬክተር ጄኔራል ጋር ተወያዩ

አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ ከጣሊያን የቱሪዝም ዳይሬክተር ጄኔራል ፍላሚና ሳንታሬሊ  ጋር ሁለቱ አገራት በቱሪዝም መስክ ትብብራቸውን በሚያጠናከሩበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ።

በውይይቱ ኢትዮጵያ ለቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን እና በቅርቡም በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል በዓመት ከ10 ሚሊየን በላይ በትራንዚት የሚያልፉትን መንገደኖች ኢትዮጵያን ጎብኝተው የሚያልፉበት ሁኔታ የተመቻቸ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም ሶስት አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻ ፓርኮች ተመርቀው ወደ ስራ መግባታውን እንዲሁም ሌሎች ሶስት መዳረሻዎችን ለማልማት በአገር አቀፍ ደረጃ በእቅድ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

በተጨማረም ጣሊያን በዘረፉ ከፍተኛ ልምድ ካካበቱ አገራት መካከል ስለምትመደብ በዘርፉ ኢትዮጵያ ያላትን አቅም ለማሳደግ የአቅም ግንባታ ስልጠና፣ ልምድና ተሞክሮ እንዲሁም የእውቀት ሽግግር ማግኘት የሚቻልበትን ሁኔታ ጠይቀዋል።

ዳይሬክትር ጄኔራሏ የቱሪዝም ዘርፍ በኮቪድ-19 ምክንያት ክፉኛ እየተፈተነ መሆኑን ገልፀው ወደ ፊት ከኢትዮጵያ ጋር ዘርፉን ለማዘመን በትብብር ለመስራት ፍላጎታቸውን እንደሆነ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፍት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

 

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

 

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

 

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version