Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቻይና ለሀምሳ ዓመታት የዘለቀውን አጋርነቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ለሀምሳ ዓመታት የዘለቀውን አጋርነቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩአን ገልጸዋል፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩአንን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ስላለው የተጠናከረ ግንኙነትና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡

አምባሳደር ዣኦ ዢዩአን ኢትዮጵያና ቻይና ሀምሳ አመታትን የዘለቀ በመተባባር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ወዳጅነት እንዳላቸው አውስተዋል፡፡

አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው ቻይናና ኢትዮጵያ የቆየ ወዳጅነትና የተጠናከረ ግንኙነት ያላቸው ሃገራት መሆናቸውን ጠቁመው፤ በኢኮኖሚው ረገድ ኢትዮጵያ ከቻይና ትልቅ ትምህርት እንደምታገኝም ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም በቅርቡ በትግራይ ክልል ስለተወሰደው የህግ ማስከበር ዘመቻ አንስተው ጉዳዩ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በቀጣይም የቻይና መንግሥት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ ያለው ወሳኝ ሚና የሚቀጥልና የበለጠ የሚጠናከር መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

አምባሳደር ዣኦ ዢዩአን ቻይና በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የማትገባ ሀገር መሆኗን ገልጸው፤ በትግራይ ክልል የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ውጤታማ ሆኖ መጠናቀቁን አንስተዋል፡፡

በቀጣይም ኢትዮጵያ ለምታደርገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ቻይና አጋር መሆኗን በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር መግለጻቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version