Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አየር መንገዱ ለመንገደኞች ተፈጥሯዊ የሀገር ውስጥ ማዕድ ማጋራት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ “በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ፤ ተፈጥሯዊ ማዕድ ይቋደሱ’’ በሚል መርህ ለተጓዦቹ ተፈጥሯዊ የሆኑ የሀገር ውስጥ ማዕድ ማጋራት መጀመሩን አስታወቀ።

አየር መንገዱ በሀገር ውስጥ አምራቾች የሚመረቱ እንደ ቡና፣ ማር እንዲሁም አትክልት እና ፍራፍሬ ተፈጥሯዊ የምግብ ግብዓቶችን ለደንበኞቹ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ነው የገለጸው።

ተቋሙ ሌሎች ግዙፍ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች የሚጠቀሙበትን ይህን ተፈጥሯዊ ማዕድ ማጋራት ልምድ በመቅሰም ወደ ተግባር መግባቱም ተጠቁሟል።

እነዚህን ተፈጥሯዊ ማዕድ ዓይነቶች የሀገር ውስጥ አምራች ድርጅቶች ለእይታ በዝግጅቱ ላይ ይዘው ቀርበዋል።

በዚህም አየር መንገዱ ወደዚህ እንቅስቃሴ መግባቱ የሀገር ውስጥ አምራቾችን በማበረታታት ተጨማሪ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር እና የውጭ ምንዛሪንም ማዳን ያስችላል መባሉን ኢብኮ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version