Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንዳንድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት በረራዎች መስተጓጎላቸውን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንዳንድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት ዛሬ ጥር 29 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ላልይበላ፣ ጎንደር እና ባህር ዳር  ይደረጉ የነበሩ በረራዎች መስተጓጎላቸውን ገለጸ፡፡

አየር መንገዱ የአየር ሁኔታው መሻሻሉን የሚገልጽ መረጃ ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት እንደደረሰው በረራውን የሚቀጥል መሆኑን ገልጿል፡፡

ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት መስሪያ ቤት መረጃ እንደደረሰውም በጥሪ ማዕከሉ በኩል ለደንበኞቹ የሚያሳውቅ መሆኑንም በፌስቡክ ገጹ ጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለተፈጠረው መጉላላትም ይቅርታ ጠይቋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version