Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሀረሪ ክልል ፣ የስልጤ ዞንና የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ፣ የስልጤ ዞንና የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች ሀገራዊ ለውጡን በመደገፍ የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግስት አመራር የመጣውን ሀገራዊ ለውጥ በመደገፍ ነው ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ የሚገኙት፡፡
በድጋፍ ሰልፉም “አሸናፊ ሐሳብን እናራምዳለን፣ ፅንፈኝነትን አምርረን እንታገለዋለን!፤ ብልፅግና የሁሉም ችግሮች መፍቻ ቁልፍ ነዉ!፤ ከብልፅግና ጋር ስኬታማ እንደምንሆን አንጠራጠርም!” የሚሉ መፈክሮችን በመያዝ ድጋፋቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡
በድጋፍ ሰልፉም በክልሉ ከገጠርና ከተማው የተወጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
እንዲሁም በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ሲሆን በድጋፍ ሰልፉ ላይ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
ሰልፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ለሰጧቸው ጠንካራ አመራር፣ በልማት መልካም አስተዳደር እንዲሁም በዲፕሎማሲ ላስመዘገቡት ድሎች እና በሶማሌ ክልል ለተመዘገበው ለውጥ ምስጋና ለማቅረብ እና በቀጣይ ህዝቡ ከጎናቸው መሆኑን ለመግለፅ ያለመ ነው።
በተመሳሳይ ሀገራዊ ለውጡን በመደገፍ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ መሆኑን ከክልሉ እና ከዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሰልፉ ”በእርሶ የሚመራው መንግስት የጀመረው የለውጥ ጉዞ ከግብ እንዲደርስ የበኩላችንን እንወጣለን””የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታን የሚያደናቅፉ የሀገር ውስጥና የውጭ ሃይሎችን እናወግዛለን” የሚሉ መፈክሮችንም አሰምተዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version