አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ተመልምለው በኢታንግ ልዩ ወረዳ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 810 ያህል የሚሊሻ አባላት ተመርቀዋል፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ቴንኩይ ጆክ እንዳሉት ÷ህግና ስርዓት መሬት ወርዶ እንዲተገበርና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ በስነ ምግባር የታነፀ የፀጥታ ሀይል ድርሻው ከፍተኛ ነው ፡፡
ተመራቂ የሚሊሻ አባላትም በስልጠናው ወቅት ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በመጠቀም ህዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃትና በታማኝነት ሊወጡ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡
በክልሉ በጠረፋማ አካባቢዎች የሚደርሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥፋትን ለመከላከልም የሚሊሻ አባላት ሰልጥነው ወደ ስራ መግባታቸው የችግሩን አሳሳቢነት እንደሚያቃልል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
መንግስት የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅና የለውጡን ጉዞ ከዳር ለማድረስም የፀጥታ ኃይሉን አቅም መገንባት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ቶማስ ቱት በበኩላቸው ህዝቡ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች በወቅቱ ምላሽ ከመስጠት ባሻገር ተቋሙን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የህግ የበላይነትን በማስከበር ለውጡን ለማስቀጠል መስራት እንደሚገባቸው አብራርተዋል፡፡
የሚሊሻ አባላቱም ሙያው የሚጠይቀውን ስነ ምግባር በመላበስና በብቃት በመወጣት ሀገራዊ ለውጡን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ሊያሸጋግሩ እንደሚገባ መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

