አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) 5ኛው የብስክሌተኞችና የእግረኞች ቀን በመላዉ የሀገሪቱ ከተሞች ተከበረ፡፡
የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር የኋላሸት ጀመረ በአዲስ አበባ ከቤቴል ሚካኤል- አንፎ ስላሴ በተካሄደዉ መርሃ ግብር ተገኝተው እንዳሉት የትራፊክ አደጋን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የእግር ጉዞና የብስክሌት ትራንስፖርትን ለማበረታታት “ከጳጕሜን እስከ ጳጉሜን እንደርሳለን!” በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረውን ንቅናቄ በማስቀጠል ዛሬ ለ5ተኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ በመከበር ላይ ነው፡፡
ሚኒስቴሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሞተር አልባ የትራንስፖርት ስትራቴጅን በመተግበርም የትራንስፖርት አማራጮችን በማስፋት ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልፀው ብዙሃኑን የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ እና አሳታፊ የሚያደርግ ጤናማ የትራንስፖርት አማራጭችን የእግር ጉዞ፣ የብስክሌት እና በካይ ያልሆኑ ትራንስፖርቶችን መጠቀም ሊበረታታ ይገባል ብለዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታዉ የሀገሪቱ ከተሞች ለእግረኞችና ሳይክል ተጠቃሚዎች ምቹና ንጹህ መንገዶችን ማዘጋጀት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
ህብረተሰቡ ደግሞ መንገዶች የሰዎች ሰላማዊ መገናኛ መድረኮች መሆናቸውን በመገንዘብ ለመንገዶች ምቾት፣ደህንነትና ንጽህና በመረባረብ የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስርዓት በአገራችን ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲስፋፋ የበኩላችንን እንወጣ ሲሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

