አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ በሁሉም ስቴቶች የሚገኙ ከ800 በላይ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የሃይማኖት አባቶች፣ የአደረጃጀት ተወካዮች፣ ምሁራን፣ የአድቮኬሲና ሌሎች አካላት በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የዙም ውይይት አካሂደዋል።
ውይይቱ በዋሺንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመላው ዓለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ ነው ትናንት ጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ነው የተካሄደው፡፡
ተሰብሳቢዎቹ ባለ 4 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ውይይታቸውን አጠናቀዋል፡፡
በዚህም በውጭ የሚኖሩ የጽንፈኛው የህወሐት ቡድን ደጋፊዎች በማህበራዊና በመደበኛ ሚዲያ አለም አቀፍ ማህበረሰቡን፣ የውጭ መንግታትንና የአለም አቀፍ ተቋማትን ለማሳሳት በትግራይ ህዝብ ስም የሚያካሂዱትን የሃሰት ፕሮፓጋንዳ እንደሚያወግዙ ገልፀዋል፡፡
ይህንን በብቃት ለመመከከትም በተደራጀ መንገድ እንሰራለን ነው ያሉት፡፡
በትግራይ ክልል እና በሌሎች የአገራችን ክፍሎች የተፈናቀሉ እና አስቸኳይ ድጋፍ የሚሹ ወገኖቻችችን ተመልሰው እንዲቋቋሙ በገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፍ እናደርጋለን ሲሉም አሳውቀዋል፡፡
ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ጋር በተያያዘ ከየትኛውም ወገን የሚነዛውን የሃሰት ፕሮፓጋንዳ አጥብቀን እናወግዛለን፤ ለግድቡ ማስጨረሻ ገንዘብ ድጋፍ ማድረጋችንን እንቀጥላለንም ብለዋል በአቋም መግለጫቸው።
በመግለጫቸው ሱዳን ከወረረችው የኢትዮጵያ ግዛት በአስቸኳይ እንድትወጣ ጠይቀዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

