Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በወልቂጤ ከተማ በመንግስትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነባ የ2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ22 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በመንግስት እና በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነባው 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤትግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ፡፡
ህንፃው ባለ 5 ወለል ሲሆን 2ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተናገድ እንደሚችልም ተገልጿል፡፡
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ገብረመስቀል ትምህርት ቤቱ በርካታ ምሁራን የፈለቁበት በመሆኑ በቀጣይም መሰል ግንባታዎችን በማስፋፋት ትምህርት ቤቱን ወደ ኮሌጅና ዩኒቨርሲቲ ለማሳደግ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም በህንጻ ግንባታ ያልተሟላ የግብአት አቅርቦት ችግሮችን ለመቅረፍ የአካባቢው ባለሃብቶች፤ ተወላጆችና ምሁራን ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል፡፡
በተያያዘም በእለቱ በወልቂጤ ከተማ የሚገኘው የራስ ዘ ስላሴ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የባለ አራት ወለል የማስፋፊያ የህንጻ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠ ሲሆን ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሰራ መገለጹን ደቡብ ሬዴዮና ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version