Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከዩ ኤስ ኤይድ ኢትዮጵያ ጋር በጋራ መስራት በሚያስችሉት ጉዳዮች ላይ መከረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከዩ ኤስ ኤይድ ኢትዮጵያ ጋር በጋራ መስራት በሚያስችሉት ጉዳዮች ላይ መከረ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ከዩ ኤስ ኤይድ ኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሺን ጆንስ እና ከሌሎች የተቋሙ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

የአይሲቲ ፓርክን በፋይናንስ እና በቴክኒክ ማገዝ ፣ በአይሲቲ ዘርፍ ኢንቨስትመንት መሳብ እና ማስተዋወቅ፣ ለኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ እና መካከለኛ የስራ ኃላፊዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ማመቻቸት እና የሶላር ታዳሽ ኃይል አቅርቦት ላይ አብሮ ለመስራት ተወያይተዋል፡፡

በቀጣይም የተቀናጀ ስራ ለመስራት የሚያግዝ የቴክኒክ ቡድን በማቋቋም ወደ ስራ ለመግባት ከስምምነት ተደርሷል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version