አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳዉሮ ዞንና የኮንታ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ::
ነዋሪዎቹ በሰልፉ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጎን በመቆም የተጀመረውን የልማት ጉዞ እናስቀጥላለን፣ የሃገራዊ ለውጡ በህወሓት ርዝራዦች አይደናቀፍም ፣ ለዓለም የሰላም ሎሬት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ልዩ አድናቆት አለን የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችን ማሰማታቸውን ከዳውሮ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ የኮንታ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ ሲሆን በሰልፉ “ፈተናዎችን በጋራ እየመከትን የለውጡን ዘላቂነት እናረጋግጣለን፣ የታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚያደናቅፉ የውስጥና የውጭ ሃይሎችን እናወግዛለን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጁንታውን ቡድን ለማምከን የሰጡትን አመራር እናደንቃለን የሚሉ መልዕክቶች በማስተጋባት ድጋፋቸውን ገልፀዋል፡፡
እንዲሁም ለውጡን የሚያደናቅፍ የሴራ ፖለቲካ እናወግዛለን፣ ለአስተዋይና ለሁሉን አቀፍ የአመራር ጥበቦ እናመሰግናለን፣ በትብብርና በድርድር መንፈስ ኢትዮጵያዊ አንድነትን እናድስ፣ ታላቁ የለውጥ ጉዞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሪነት ተጠናክሮ ይቀጥላል” የሚሉ መልእክቶችንም አስተላልፈዋል፡፡
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

