አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በጋምቤላ ክልል የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚግዝ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያገለግሉ 5 የፅኑ ህሙማን አልጋዎች፣ 50 የተሞሉ የኦክሲጂን ሲሊንደሮችና 300 የህክምና ባለሙያዎች የመከላከያ ልብሶች መሆናቸው ታውቋል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በርክክቡ ወቅት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስነ ህይዎታዊ አፈጣጠሩን ከመለዋወጥ ጋር ተያይዞ ቫይረሱ እንደ አዲስ እየታየ መምጣቱን አንስተዋል።
በክልሉ የሚደረገውን የቫይረሱን መከላከል እንቅስቃሴ ስኬታማ ለማድረግም የፌደራል መንግስትና የባለድርሻ አካላት ትብብርና የጋራ ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ያደረገው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በጋምቤላ አጠቃላይ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገው እንቅስቃሴ እንደሚያግዝ ተናግረዋል ።
ለተደረገው ድጋፍም በክልሉ መንግስትና በራሳቸው ስም ምስጋና ማቅረባቸውን ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

