Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጀርመን ከምርጫ ጋር በተያያዘ የ191 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመን መንግስት በፈረንጆቹ ከ2020 እስከ 2025 ባለው የምርጫ ሂደት ዘመን በአውሮፓ ኮሚሽን አማካኝነት በኢትዮጵያ ውጤታማ የምርጫ አስተዳደር እና አመራር እንዲኖር የሚያስችል የልማት ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ፡፡

የተደረገው ድጋፍ 4 ሚሊየን ዩሮ ወይንም 191 ነጥብ 58 ሚሊየን ብር ሲሆን ለኢትዮጵያ መረጋጋት፣ ሰላምና ብልፅግና አስተዋፅዖ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡

ይህ የገንዘብ ድጎማ ስምምነት በፈረንጆቹ ታህሳስ 6 ቀን 2019 በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ቡድን አምባሳደር ጆሃን ቦርግስታም መካከል የተፈረመው የ11ኛው የአውሮፓ ልማት ፈንድ ብሔራዊ ፕሮግራም አካል ነው ተብሏል፡፡

በጀርመን መንግሥት እና በአውሮፓ ህብረት በኩል በአውሮፓውያኑ ህዳር 26 ቀን 2020 ለኢትዮጵያ 10 ሚሊዮን ዩሮ ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት ተደርሶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ከ2020 እስከ 2025 የምርጫ ሂደት ውስጥ በኢትዮጵያ ውጤታማ የምርጫ አስተዳደር እና አመራር እንዲኖር ጀርመን እና የአውሮፓ ህብረት አጠቃላይ 24 ሚሊዮን ዩሮ (1 ነጥብ 49 ቢሊዮን ብር) የድጋፍ ማድረጋቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በ1964 የጀመረው የሁለቱ ሀገራት መደበኛ የልማት ትብብር በጋራ መከባበር እና መተማመን ላይ የተመሠረተ የቆየ ግንኙነት ሲሆን ጀርመን ከ1957 ጀምሮ ለኢትዮጵያ የቴክኒክ ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷ ይታወቃል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version