Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በዘንድሮው አመት 60 ሺህ ሄክታር ቡና ለመጎንደል እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን ከግብርና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማትና ከጅማ ዞን አመራሮች ጋር በጅማ ዞን የቡና ጉንደላ ስራን ጎበኙ።

የግብርና ሚኒስትሩ የቡናን ምርታማነት ለመጨመር ያረጀ ቡናን መጎንደል እና ነቅሎ በምትኩ አዳዲስ የቡና ችግኞች ተከላን የማስፋፋት ስራ በቡና አብቃይ ክልሎች ላይ የትኩረት አቅጣጫ ተደረጎ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ይህ በጅማ ዞን አርሶ አደሮች፣ በትራኮን ትሬዲንግ የለማ የቡና ማሳ እና በህብረት ስራ ማህበራት እየተደረገ ያለው ተሞክሮ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲሰፋ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ሚኒስቴሩ መስሪያቤቱ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ በበኩላቸው እንደ ሀገር ካለው ቡና 67 በመቶ ያረጀ እና ምርታማነቱ እየቀነስ ያለ በመሆኑ ባለፉት ሁለት አመታት ከ200 ሺህ ሄክታር በላይ የጉንደላ (እደሳ) ስራ የተሰራ ሲሆን በዘንድሮ አመትም 60 ሺህ ሄክታር ቡና ለመጎንደል እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version