አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ሴኔት የሀገሪቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የተጀመረው የክስ ሂደት ህገመንግስታዊ ነው ሲል ወሰኗል፡፡
የትራምፕ ጠበቆች በበኩላቸው የስልጣን ዘመናቸው ካበቃ በኋላ መጠየቅ የለባቸውም በማለት ተከራክረዋል፡፡
ሴኔቱ 56 ለ 44 በሆነ የድምጽ ብልጫ ነው የክስ ሂደቱን እንዲቀጥል የወሰነው፡፡
ትራምፕ ክስ የቀረበባቸው ባለፈው ወር አመጽን አነሳስተዋል በሚል ነው፡፡
100 አባላት ባሉት በዚህ ሴኔት የክስ ሂደቱ በሪፐብሊካኖችም ድጋፍ አግኝቷል፡፡
በዚህ ሂደት ትራምፕ ጥፋተኛ የሚባሉ ከሆነ ድጋሚ ለፕሬዚዳንትነት የመወዳደር ዕድላቸውን ያጣሉ ተብሏል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

