Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የማላዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ተባብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማላዊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ተባብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ፡፡

የሚሲዮኑ ምክትል መሪ አምባሳደር ሲራጅ ረሺድ ከማላዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ ዶክተር ሉኪ ሲክውዜ ጋር  መክረዋል፡፡

በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ህግን ለማስከበርና የጁንታውን ኃይል ወደ ፍትህ ለማቅረብ የተካሄደው ዘመቻ መጠናቀቁን ገልጸው በአሁኑ ወቅት መልሶ ግንባታና ወንጀለኞችን አድኖ ለፍትህ ማቅረብ ላይ መንግስት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ከማላዊ  መንግስት ጋር  በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በፊት በ2017 የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን የተካሄደ ሲሆን ቀጣዩን የጋራ ኮሚሽን ለማካሄድ በ2019 የነበረው በኮሮናና በተለያዩ ምክንያቶች ያለመካሄዱ ነው የተጠቀሰው፡፡

የሁለቱን መንግስታት ግንኙነት ለማጠናከርና በኢኮኖሚና በማህበራዊ ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደዚሁም በሰላምና ፀጥታ አብሮ ለመስራት፣ በዲፕሎማሲና በፖለቲካ ዘርፍ ለመመካከር እንዲቻል የተለያዩ የመግባቢያ ስምምነቶችን ለማካሄድ ሂደት ላይ እንደሚገኙም ተጠቅሷል፡፡

የማላዊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ ዶክተር ሉኪ ሲከውዜ የኢትዮጵያ መንግስት ህግን ለማስከበር ያካሄደውን ዘመቻ በቅርበት ሲከታተሉ እንደነበርና በአጭር ጊዜ ውስጥ መጠናቀቁ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያና ማላዊ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆኑ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከርና የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ተጠቃሚ ለማድረግ ማላዊ ከኢትዮጵያ ተቀራርባ እንደምትሰራ አብራርተዋል፡፡

የጋራ ኮሚሽን እንዲካሄድም የሀገራቸው ሙሉ ፍላጎት መሆኑንና ከወዲሁ ስምምነቶቹ ለፊርማ እንዲዘጋጁ እንደሚሰሩም ነው የገለጹት፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የጀመራቸው ለውጥ ፕራይቬታይዜሽን ሌሎች መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እንዲሳካ ምኞታቸው መሆኑንም መግለጻቸውን በኬንያ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version