Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የድምፅ ብክለት የሚፈጥሩ ድርጅቶች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የድምፅ ብክለት በሚያደርሱ ቡቲኮች የመንገድ ላይ ማስታወቂያዎች እና ሌሎች በህብረተሰቡ ላይ የደምፅ ብክለት የሚፈጥሩ ድርጅቶች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ እርምጃ ሊወሰድ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን ከክፍለ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ አመራሮች ጋር ውይይት በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት አካሄዷል፡፡

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወይሳ ፈይሳ በህብረተሰቡ ላይ የደምፅ ብክለት የሚፈጥሩ ድርጅቶች እና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ ከክፍለ ከተሞች ጋር በመቀናጀት የክትትል እና ቁጥጥር እንዲሁም እርምጃ የመወሰድ ስራ እንደሚጀመር በውይይቱ የገለጹት፡፡

የአካባቢ ብክለት እና የአየር ንብረት ለውጥ ዳይሬክቶሬት ዘርፍ በቀጣይ ስለሚኖሩ ቅንጅታዊ አሰራሮች ላይ እንዲሁም በክትትል እና ድጋፍ ዙሪያ መሰራት ስላለባቸው ስራዎች እና ስላሉ ክፍተቶች ሰፊ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ከሃይማኖት ተቋማት የሚለቀቁ የድምፅ ብክለቶች ላይ የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን መስሪያ ቤት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ በመሆን የዳሰሳ ጥናት እንደሚያካሂድ ነው የጠቀሱት፡፡

በተጨማሪም ችግሩ ያለበትን ደረጃ የመረዳት እና በቀጣይም ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጋር በመነጋገር እና የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የማስተካከል ስራ እንደሚሰራ አቶ ወይሳ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ባለፉት ስድስት ወራት በማዕከል እና በክፍለ ከተማ ጥምረት ከ2ሺህ በላይ አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ክትትልና ቁጥጥር መደረጉንም ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

የድምጽ ብክለት፣ በፍሳሽ ብክለት፣ በደረቅ ቆሻሻ እና ፕላስቲክ አምራች ድርጅቶች ላይ በአካባቢ ላይ ብክለት በማድረሳቸው ምክንያት አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version