Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ከግብጽ የውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ጋር በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ከግብጽ የውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ሼሪፍ ኢሳ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው ወቅትም አምባሳደር ማርቆስ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የኢትዮጵያን አቋን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ ከተፋሰሱ ሃገራት ጋር ያላትን ልዩነት በንግግር ለመፍታት ያላትን ዝግጁነት በተመለከተም ገልጸዋል።

የግብጽ የውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ሼሪፍ ኢሳ በበኩላቸው ሃገራቸው ከግድቡ ጋር በተያያዘ ያሉ ልዩነቶችን በድርድር ለመፍታት ያላትን ዝግጁነት ለአምባሳደር ማርቆስ ገልጸውላቸዋል።

አምባሳደሮቹ በውይይታቸው ወቅት የኢትዮጵያን እና የግብጽን የሁለትዮሽ ግንኙነት በተመለከተ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም የሃገራቱን ታሪካዊ ግንኙነት ማጠናከር የሚያስችል ማዕቀፍ መተግበር በሚቻልበት አግባብ ላይም መክረዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version