አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአንኮበር በተከሰተ የመኪና አደጋ የስድስት ሰዎች አለፈ፡፡
አደጋው ዛሬ ሌሊት ከሀርአምባ ወደ አንኮበር ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የጭነት ተሽከርካሪ በሀርአምባ ቀበሌ ልዩስሙ ልጄን አደራ በተባለ ቦታ ሲደርስ በመገልበጡ ነው፡፡
በአደጋው በጭነት መኪናው ላይ ተሳፍረው ከነበሩት ሰዎች ውስጥ እስካሁን የስድስት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
በአደጋው በ30 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱን ከአንኮበር ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ጎረቤላ ጤና ጣቢያ ተወስደው እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

