አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት በኢትዮጵያ ለ1 ነጥብ 7 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን የስራ ዕድል ፈጠራ ብሄራዊ ምክር ቤት አስታወቀ።
የስራ ዕድል ፈጠራ ብሄራዊ ምክር ቤት በጠራው መድረክ ላይ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽነር አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንደገለፁት በግማሽ አመቱ የተፈጠረው የስራ እድል ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ49 በመቶ ብልጫ አለው ብለዋል።
በግማሽ አመቱ የስራ እድልን በግብርናው ዘርፍ 44 በመቶ፣ ኢንዱስትሪ 32 በመቶ፣ በአገልግሎት ዘርፍ 24 በመቶ የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ የአግልግሎት ዘርፍ 44 በመቶ የስራ እድል በመፍጠር ቀዳሚ መሆኑን ተናግረዋል።
ግብርናው ዘርፍ 30 በመቶ የስራ እድል በመፍጠር ከእቅዱ ዝቅ ያለ አፈጻጸም ታይቶበታልም ነው ያሉት።
በስድስት ወሩ በየደረጃው ያሉ አካላት ተናቦ አለመስራት፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽ አለመሆን፣ የስራ እድል ፈጠራው አካታች አለመሆን እና የብድር አቅርቦትና አመላለስ ላይ ያለ ክፍተት ያጋጠሙ ችግሮች ማሆናቸው ተገልጿል፡፡
በብስራት መለሰ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

