Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ የሚውል የ400 ሚሊዮን ብር የድጋፍ ስምምነት ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ጤና ቢሮ የተናቀናጀ የጤናና የልማት አገልግሎት ድርጅት (ISHDO) ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ ለማድረግ የ400 ሚሊዮን ብር የድጋፍ ስምምነት አደረገ።

ድጋፉ እድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሆናል ተብሏል።

እንደ ኢቢሲ ዘገባ ፕሮጀክቱ  ለሶስት አመታት የሚቆይ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል በ41 ወረዳዎች እና ከተሞች ላይ እንደሚተገበር በዝግጅቱ ተጠቅሷል።

የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መንግስቱ በቀለ በስምምነቱ ላይ እንደተናገሩት÷ የድጋፍ ስምምነቱ ለታለመለት ዓለማ እንዲውል ይደረጋል።

በዚህ የድጋፍ ስምምነት ላይ የመንግስት ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version