Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጉምሩክ ኮሚሽን ዘመናዊ የመረጃ ልውውጥ ስርዓትን መተግበር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን እና ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዘመናዊ የመረጃ ልውውጥ ስርዓትን መተግበር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቀበታ መረጃን በአግባቡ መያዝ፣ መለዋወጥና መተንተን ከተቻለ አገልግሎት አሰጣጥን የተሻለ ከማድረግም ባለፈ ህገ-ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ ስርዓት ለማስገባት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ ስምምነቱ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽኑ በመረጃ አያያዝና ልውውጥ በሀገር ውስጥ ከሚገኙ መንግስታዊ ተቋማት በተጨማሪ ከቻይና ጉምሩክ ጋር መረጃ ለመለዋወጥ ስምምነት ተፈራርሞ ወደተግባር እንደገባም ኮሚሽነሩ አንስተዋል፡፡
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳር ምስጋኑ አርጋ በበኩላቸው ዘመናዊና ጥራቱን የጠበቀ መረጃ ለሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ ዕድትና ማህበራዊ መስተጋብር ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ ማንኛውም ተቋምና ግለሰብ ለመረጃ ያለው አስተሳሰብ መሻሻልና መዘመን አለበት ማለታቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version