አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሳሪስ አደባባይ አካባቢ የድምፅ ብክለት ያደረሱ ስድስት መጠጥ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች ታሸጉ፡፡
የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን ከዚህ ቀደም ከ200 በላይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው እንደነበር አስታውሷል፡፡
አሁን የታሸጉት ድርጅቶችም የእርምት እርምጃ ባለመውሰዳቸው መሆኑን የኮሚሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዩች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙክታር ሰኢድ ተናግረዋል፡፡
መጠጥ ቤቶቹ ከተፈቀደው 45 ዴሲቤል የድምፅ መጠን በላይ አልፍው እስከ 85 ዴሲቤል መጠን ሲጠቀሙ መቆየታቸውን በጥናት መረጋገጡንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም በአካባቢ ላይ ብክለት የሚያደርሱ ኢንዱስትሪዎች፣ ፋብሪካዎች፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት መጠጥ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች ላይ ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቁን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

