Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጋምቤላ ክልል ከሙቀት ጋር ተያይዞ የመንግስት የሥራ ሠዓት ለውጥ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የሙቀቱ መጠን እየጨመረ በመምጣቱ የመንግስት የሥራ ሠዓት ለውጥ መደረጉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ፒተር ሆዎ እንደገለጹት የሙቀቱ መጠን እየጨመር በመምጣቱና ለስራ አመቺ ባለመሆኑ ከየካቲት 3 ቀን 2013ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት የሚቆይ ጊዜያዊ የመንግስት ሥራ ስዓት ለውጥ ተደርጓል።
በለውጡ መሰረትም ቀደም ሲል በመደበኛው የሥራ ስዓት ከጠዋቱ አንድ ሠዓት እስከ ስድስት ሠዓት ተኩል የነበረው ከአንድ ሠዓት እስከ አምስት ሠዓት ተኩል እንዲሆን ተወስኗል።
እንዲሁም ከሠዓት በኋላ ከዘጠኝ ሠዓት እስከ አስራ አንድ ሠዓት ተኩል የነበረው ከአስር ሠዓት እስከ አስራ ሁለት ሠዓት ተኩል እንዲሆን መወሰኑን ኃላፊው አስታውቀዋል።
የስራ ሠዓት ለውጡ ወይናደጋ የሆነውን የማጃንግ ዞን እንደማይጨምር ጠቁመው የመንግስት ሠራተኞች በተጠቀሰው ጊዜ ወደ ቢሮ በመግባት የተለመደውን ሥራቸውን እንዲያከናኑ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።
በብሔራዊ ሜትሮዎሎጂ ኤጀንሲ የጋምቤላ ክልል አገልግሎት ማዕከል መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ወቅት የክልሉ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 40 ነጥብ 4 ዲግሪ ሴልሽየስ፣ የሌሊቱ ደግሞ 16 ነጥብ 6 ዲግሪ ሴልሽየስ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version