Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ መቀመጫቸውን ታንዛኒያ ካደረጉ የአፍሪካ ሃገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ መቀመጫቸውን ታንዛኒያ ካደረጉ የኬንያ፣ የአንጎላና የሞሮኮ አምባሳደሮች ጋር የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ያካሄደችውን የህግ ማስከበር ዘመቻ እና ዘመቻው መጠናቀቁን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በክልሉ እየተሰሩ የሚገኙ የመልሶ ማቋቋም ስራዎችን በተመለከተ ለአምባሳደሮቹ ገለፃ ተደርጓል።
እንዲሁም በክልሉ ሰብዓዊ ድጋፍ በመንግስት እና በዓለም አቀፍ ዕርዳታ ሰጭ ድርጅቶች አማካኝነት እየተሰጠ እንደሚገኝ አምባሳደሩ አብራርተዋል።
በተጨማሪም በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እና የኢትዮጵያን አቋም እንዲሁም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ያሉ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ማስረዳት መቻሉን ከታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version