አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የተመራ ቡድን በመተከል ዞን ከቀያቸው ተፈናቅለው በቻግኒ ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃዮችን ጎብኝቷል፡፡
በጉብኝቱ ቡድኑ በመጠለያው የተለያዩ ድጋፎች በህብረተሰቡ እየተደረገ መሆኑን የተመለከተ ሲሆን ሁሉም የተለመደውን ድጋፍና ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እንደተናገሩት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ገልፀው ድጋፉ ለወገን አለኝታነትን ለማሳየት የተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወይዘሮ እታገኘሁ አደመ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ሁሉም በዚህ መልኩ ከተባበረ የማንወጣው ፈተና የለም ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details…
በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

