Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በዋግኽምራ ዞን 150 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ድሃና ወረዳ 150 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመርቋል።

በምርቃቱ ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሞ ማሞና የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮን ጨምሮ የክልልና የብሔረሰብ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ፕሮጀክቱ ከ34 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑም ተመላክቷል።

በዚህም የባርግባ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት በድሃና ወረዳ አምደወርቅ ከተማን ጨምሮ ጭላ፣ ጋኪው፣ ብርብራ እና ሽማምዳ የተሰኙ የገጠር ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።

ከዋን ወሽ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በ120 ሚሊየን ብር መነሻ የተጀመረው ፕሮጀክት ተጨማሪ የትራንስፎርመር እና ሌሎች ወጪዎች ተጨምረውበት እስከ 150 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ ከድሃና ወረዳ ዋና ከተማ አምደወርቅ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባርግባ ወንዝን በመሳብ የተሠራ መሆኑን አብመድ ዘግቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version