አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ከተሞች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን እና የለውጥ አመራሩን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ፡፡
በደሴ፣ በኦሮሞ በሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከሚሴ እና ባቲ ከተሞች በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን እና የለውጥ አመራሩን የሚደግፍ ሰልፍ የተካሄደው፡፡
የድጋፍ ሰልፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን እና መላውን የለውጥ አመራር ለማበረታታት ያለመ ነው ተብሏል፡፡
በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በመውጣት በኮምቦልቻ ከተማ ስታዲየም በመገኘት በደማቅ ሁኔታ የድጋፍ ሰልፉን እያደረጉ እንዳለ ነው የተነገረው፡፡
ሰልፈኞቹ “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን እንደግፋለን ፣ ለውጡን ሊቀለብሱ የሚፈልጉ ኃይሎችን እንቃወማለን” የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ድጋፋቸውን ገልፀዋል፡፡
በአጭር ጊዜ በየዘርፉ አንፀባራቂ ድሎችን እያስመዘገበ የሚገኘው የለውጥ ጉዞ በተለያዩ ኃይሎች እንዳይደናቀፍ ተግቶ መጠበቅና ከዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጎን መቆም እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን የሚያደናቅፉ የውስጥና የውጭ ኃይሎችን እናወግዛለን፣ አደናጋሪ አጀንዳዎችን በማክሸፍ የተጀመረውን ለውጥ እናስቀጥላለን፣ ታላቁ የለውጥ ጉዟችን በጠቅላይ ሚኒስተሩ መሪነት ተጠናክሮ ይቀጥላል የሚሉ መፈክሮች በሰልፉ ተሰምተዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ህብረተሰቡ በሃገሪቱ እየተመዘገበ ያለውን የለውጥ ተግባር የሚያደንቁ ሃሳቦች አንፀባርቋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

