Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሩሲያ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ፣ የንግድ እና  የቱሪዝም ሀብቶችን የሚያስተዋወቅ ፎረም ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሩሲያ ቱሜን ክልል ለተውጣጡ ባለሀብቶች፣ ነጋዴዎች፣ እና ለከልሉ መንግስት የኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ኃላፊዎች ሀገራችን ስላላት የኢንቨስትመንት፣ ንግድ እና ቱሪዝም ሀብቶች የማስተዋወቂያ ፎረም  በበየነ መረብ  ተካሄዷል፡፡

በፎረሙ ላይ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ስለኢትዮጵያ የንግድና የኢንቨስትመንት አቅም ገለጻ አድርገዋል።

በተጨማሪም ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ከውሀ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከንግድ እና ዘርፍ ማህበራት መስሪያ ቤቶች የተወከሉ ተሳታፊዎች ስለኢትዮጵያ  የኢንቨስትመንት እና የንግድ አቅም እና ሀብቶች ገለፃ አድርገዋል፡፡

በሩሲያን በኩል ከተሳታፊዎቹ መካከል የሆኑት የቱሜን ክልል የኢንቨስትመንት ፖሊሲና ድጋፍ ጄነራል ዳይሬክተር የሆኑት ማሹኮቭ አንቶን አድንሬቪች ፣ የሪጅኑ የንግድና የኢንቨስትመንት አካላት እንዲሁም በአገራችን የሩሲያ ኤምባሲ ዲፕሎማት በፎረሙ የተደረገላቸው ገለፃ  በኢትዮጵያ ስላለው የንግድ፣ የኢንቨስትመንት፣ የቱሪዝም ሀብቶች ግንዛቤ እንዳስጨበጣቸው ገልጸዋል።

በዚህም ከኢትዮጵያ ጋር የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ለመመስረት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የአፍሪካ ሕብረት የንግድ እና የኢንዱስትሪ እንዲሁም የጤና ክፍሎች ተወካዮች በመገኘት ሕብረቱ በንግድ እና በኢንዱስትሪ እንዲሁም በጤና ዘርፍ እያከናወነ ስላለው ተግባር ማብራራታቸውን ሞስኮ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version