Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኮሚሽኑ ሙስና ከመፈጸሙ በፊት ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስትና የህዝብ ሀብት ከመዘረፉ በፊት ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን የፌደራል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።

የመንግስት ተቋማት የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች የግማሽ አመት የስራ አፈጻጸም ግመገማ መድረክ ዛሬ በባህርዳር ከተማ ተጀምሯል ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ጸጋ አራጌ ሙስናና ብልሹ አሰራርን መከላከል የሁሉም ሀላፊነት መሆኑን ገልጸዋል።

ሙስናን በተቀናጀና በተደራጀ አግባብ መከላከልና ማስቆም ካልተቻለ ሀገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ እንደምትጎዳም ተናግረዋል።

“ለዚህም ኮሚሽኑ ሙስና ከመፈጸሙ በፊት ለማስቆምና ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ ነው” ብለዋል።

በሀገሪቱ በ537 ተቋማት የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች እንዲዋቀሩ በማድረግ ሙስና ከመፈጸሙ በፊት የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የተሻሻሉ አሰራሮችን በመተግበር ሙስናን ከምንጩ ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ ለውጤታማነቱ የባለድርሻ አካላት ተሳተፎና ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑንም አመላክተዋል።

በባህርዳር ለሶስት ቀን በሚቆየው መድረክ የፌደራል፣ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲዎች የስነ ምግባር መከታተያ ባለሙያዎችና ባለድርሻዎች እየተሳተፉ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version