Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጋምቤላ ክልል የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማሳለጥ የሚያግዙ 46 ተሽከርካሪዎች ርክክብ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማሳለጥ የሚያግዙ 46 ተሽከርካሪዎች ርክክብ ተካሄደ፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ተሸከርካሪዎቹ በክልሉ የሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማከናወን ያግዛሉ ብለዋል፡፡
ተሽከርካሪዎቹ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩ ይገባልም ነው ያሉት፡፡
የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡቦንግ ኡቶው በበኩላቸው በ78 ሚሊየን 631 ሺህ 41 ብር ወጪ የሆነባቸው 46 ተሽከርካሪዎች መሆናቸውን ጠቁመው ከእነዚህ ውስጥ 12 ደብል ፒካፕ፣ 18 ሲንግል ፒካፕና 16 ሀርድ ቶፕ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡
ተሽከርካሪዎቹ የተገዙት በክልሉ በድንበር አካባቢ የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮች ላይ ፈጥኖ ለመድረስና ለመከላከል መሆኑን ጠቅሰው ከፀጥታ ጎን ለጎንም የልማት ስራዎችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማከናወን ታስቦ እንደሆነ መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version