አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ለውጡን በመደገፍ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማና የኪ ወረዳ የድጋፍ ሠልፍ ተካሂዷል፡፡
ሰልፈኞቹ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጎን በመሆን ቀጣዩን የሀገሪቱን ብልፅግና እውን እናደርጋለን፣ በመደመርም ሀገራችንን እንገነባለን፣ የአካባቢያችን ህዝብና መንግሥት በሃገራችን እየተደረገ ያለውን የህግ ማስከበር ሥራን በፅኑ እንደግፋለን የሚል መፈክር አሰምተዋል፡፡
‘ለዉጡን እንደግፋለን የሴራ ፖለቲካን እናወግዛለን’ የሚሉና ሌሎች ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ልማት ሠላምና ዴሞክራሲን የሚያወሱ የድጋፍ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።
በድጋፍ ሠልፉ ላይ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አልማው ዘውዴ እንደገለጹት፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት ለሃገሪቱ ሠላም ልማትና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እንዲሁም የጁንታውን ሃገር የማፈራረስ አጀንዳ በመቀልበስ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ላሳዩት በሳል አመራር በህዝብ ስም ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።
ለውጡን በፀና መሠረት ላይ ለማቆም የዞኑ ህዝብ ከመንግሥት ጎን እንዲቆምና በአንድነትና በወንድማማችነት ስሜት ሁለንተናዊ አስተዋፅኦውን እንዲያበረክት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በዞኑ እየታየ ያለውን ሠላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በተስፋዬ አይጠገብ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

