አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ካቢኔ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ።
የክልሉ ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለመደገፍ የ12 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረግ በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ መክሯል።
በዚህም መሰረት 10 ሚሊየን የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ እንዲሁም በትግራይ ክልል ለሚገኙ የተጎዱ ዜጎች የሚሆኑ 2 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ መጠን የሚገመት 70 ቦንዳ አልባሳት፣ 300 ኩንታል የምግብ ዱቄት እና የተለያዩ መጠን ያላቸው ሌሎች ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ ድጋፍ እንዲደረግ ካቢኔው በሙሉ ድምፅ ወስናል።
ካቢኔው በተጨማሪም በትግራይ ክልል ያለው የጤና የአገልግሎት ለመደገፍ አንድ አንቡላንስ ተሽከርካሪ እና የጤና ባለሞያዎች ቡድን ወደ ስፍራው ለመላክ ወስኗል።
በሀረሪ ክልል ደረጃ የተዘጋጀውን ድጋፍ ወደ ስፍራው የሚያደርስ የልዑካን ቡድን በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ትግራይ ክልል እንደሚያቀናም ከሀረሪ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

