Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቻይና  ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአፍሪካ ሀገራት የኮቪድ 19 የክትባት ድጋፍ ልታደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአፍሪካ አገራት የኮቪድ 19  የክትባት ድጋፍ  ልታደርግ መሆኑን በኢትዮጵያ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ አስታወቀ።

ይህም የቻይናው  ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የኮቪድ 19 ክትባቶችን ለአለም አቀፍ የህዝብ ተጠቃሚነት ለማዋል የገቡትን ቃል ለማክበር ተጨባጭ እርምጃ ነው ሲል ኤምባሲው ለፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት በላከው  መግለጫ አስታውቋል ፡፡

ወረረሽኙ  አሁንም በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ ባለበት ወቅት የኮቪድ 19 ክትባቶች የዓለም አቀፍ ትብብር ትኩረት ሊሆኑ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

በዚህም ቻይና የኮቪድ 19 ክትባት  ትብብርን በማጠናከር ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገልጿል።

የኮቪድ ክትባቱ  በሁሉም ሀገሮች ላሉ ሰዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ  እንዲሆን ይሰራልም ነው ያለው።

የዓለም ጤና ድርጅት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ቻይና ለታዳጊ አገሮችን 10 ሚሊየን ዶዝ የኮቪድ ክትባት  ለመስጠት ወስናለችም ነው ያለው መግለጫው ፡፡

ተጨማሪም ቻይና እስካሁን ጥያቄ ላቀረቡ 53 ታዳጊ አገራት የክትባት ዕርዳታ የሰጠች ሲሆን ክትባቱን ወደ 22 አገራት መላኳም ነው የተገለጸው ፡፡

ኤምባሲው በመግለጫው አያይዞም ቻይና እና ኢትዮጵያ በጥሩም ሆነ በመጥፎ ጊዜ  በትብብር የሚሰሩ የቅርብ ሀገሮች ናቸው ብሏል፡፡

በዚህም ኮቪድ 19 ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ሁለቱ እህትማማቾች ሀገሮች እርስ በእርሳቸው ሲደጋገፉ እንደነበርም ገልጿል ፡፡

ቻይና ኢትዮጵያ ቫይረሱን ለመዋጋት እንዲረዳት የህክምና ቁሳቁሶችን ከመለገስ  ባለፈ የህክምና ባለሙያዎችን  መላኳን አስታውሶ ÷ የክትባት ድጋፉም   የኢትዮጵያ መንግስት የበሽታውን ስርጭት ለመግታት እያደረገ ያለውን ጥረት ለማሳደግ ሌላ ተጨባጭ እርምጃ መሆኑን አመላክቷል፡፡

ከዚያም ባለፈ ቻይና በአለም አቀፍ  የኮቪድ-19 ክትባት  ትብብር ላይ ምንም ዓይነት የጂኦ-ፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ  ጥቅማጥቅሞችንና  ትርፍን ለማግኘት አታስብም ነውያለው።

በመሆኑም የቻይና መንግስት ሁል ጊዜ የክትባት ደህንነት እና ውጤታማነት በዋናነት  ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውንም አመልክተዋል ፡፡

ቻይና  ወረርሽኙን ለመከላከል በሚደረገው ዓለም አቀፍ ትግል የመጨረሻውን ድል ለመጎናጸፍ ከሁሉም ዓለም አቀፍ  አካላት ጋር በትብብር መስራቷን እንደምትቀጥል የቻይና ኤምባሲ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version